
አድራሻ
- አዲሰ አበባ ኢትዮጵያ
- michubetmedia@gmail.com
- +(251) 911646441
- www.michubet.com
ልጆችን የተመጣጠነ ምግብ ለመመገብ፣ የአመጋገብ ሥርአትን ለማስተማር፣ ስለ ምግብ ማወቅን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን የያዘ ጠቃሚ ኩነት ነው። ይህ ኩነት በየአመቱ ጥቅምት እና የካቲት የመጀመሪያ ሳምንት ይካሄዳል።
በቤት ውስጥ ሥራ እና በደጅ በቅጥር ወይም በግል ሥራ ላዩ ያሉ እናቶችን ለማነቃቃት፣ ለማገዝ፣ ለማስተማር እንዲሁን የግንዛቤ ለውጥ ለማምጣት በየሦስት ወሩ የሚዘጋጅ ልዩ ዝግጅት ነው።
ይህ ኩነት ከጡት ማጥባት፣ ከጡት ወተት፣ ከጨቅላ ህፃናት ጤና እና ከእናቶች ጤና ጋር የተያያዙ ጉዳዬችን የሚዳስስ እና በየአመቱ ሐምሌ መጨረሻ ላይ የሚካሄድ ነው።
ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዬች የሚስተናገዱበት ልዩ መድረክ ነው። ይህም በአመቱ መጨረሻ ይካሄዳል።
በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተሰማርተው የነበሩ ሴቶች፤ መምህራን፣ ጋዜጠኞች፣ ፀሐፊ፣ አስተዳዳሪ የጤና፣ የስነ ልቦና፣ የሂሳብ ስራ ባለሙያ፣ ዘርዝሬ በማልጨርሳቸው ሙያዎች ላይ የነበሩ ሴቶች በልጅ መውለድ ምክንያት ከስራቸው እና ከትምህርታቸው ይስተጓጎላሉ፡፡ ለቤተሰባቸው እና ለሀገራቸው ያበረክቱት የነበረው ነገርም ይገደባል፡፡ ከሁሉ በላይ ሴቲቱ የነበራት ህልም ለራሷ ልታሳካው ያሳበችው ግብ ያቆማል፡፡ “እንዲህ መሆን እፈልጋለሁ” ብላ የተመኘችው ነገር ሁሉ በጅምሩ ይቀራል፡፡ ለምን? ልጅ መውለድ ይህን የእሷን ምኞት እና ፍላጎት ማስቀረት አለበት? አንዲት አገር እናቶችን ቤት በማስቀመጥ በወንዶች እና በጥቂት ሴቶች ስራ ብቻ ማደግ ትችላለችን? ኑሮ እንዲህ እለት ተእለት በተወደደበት በዚህ ጊዜ በአንድ አባወራ ደመወዝ ብቻ ለልጆች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት ይችላል? ለሁሉም ጥያቄዎች መልሱ አይቻልም ነው፡፡ ስለዚህ ምን ይደረግ? ሰው እንዳአቅሙ ነውና፤ አገራችን የሞላት የደላት ባትሆንም ቅሉ እንደአቅሟ ለነዚህ እናቶች የድርሻዋን መወጣት ይኖርባታል፡፡ በአሁን ወቅት በስራ ገበታ ላይ ያለች ሴት የምታገኘው የወሊድ ፈቃድ በግል ድርጅቶች ሶስት ወር በመንግስት መስሪያ ቤቶች ደግሞ አራት ወር ነው፡፡ ይህ ሶስት ወይም አራት ወር ለእናትየውም ሆነ ለጨቅላው በቂ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የወሊድ ፈቃድ ወደ ስድስት ወር እንዲራዘም እና ደመወዟን እያገኘች ህፃኑን ስድስት ወር እስኪሆነው ድረስ በህክምና ባለሙያዎች እንደታዘዘው ጡት እንድታጠባው እና እሷም በደንብ ሰውነቷ እስኪጠገን በቤቷ እንደትቆይ የሚያስችላትን ፈቃድ ማግኘት አለባት፡፡ ይህ ለጤናማ ህፃንና ለጤናማ እናት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ጤናማ ህፃን ማሳደግ ማለት ጤናማ ትውልድ መተካት ማለት ነው፡፡ የእናት ጤና ማጣት፤ የስነልቦና እና የአካላዊ ጤና መጓደል በአንድ ቤተሰብም ሆነ በአገር ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ “የውሀ ጠብታ እያደር ድንጋይ ይበሳል” እንደሚባለው ይህ የወሊድ ፈቃድ አንድ የውሀ ጠብታ ሆኖ የእናቶችን፣ የቤተሰብን እንዲሁም የአገርን ደረጃ ያሻሽላል፡፡ ይህንን እንቅስቃሴ እውን ለማድረግ እና ግንዛቤ ለመፍጠር የተከፈተውን “ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ ለእናቶች” የሚለው ገፅ ደጋፊዎች በመሆን ገፁንም ለሌሎች ወዳጆቻችሁ በማካፈል እንዲሁም ገፁን እንዲመለከቱት በመጋበዝ ሀሳባችንን እንዲሳካ ታግዙን ዘንድ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡ እስካሁን ድረስ ይህን ሀሳብ በመደገፍ እና ገፁን በማካፈል ሌሎች እንዲያውቁት ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡
በልጆች እና በወላጆች መካክል፣ በልጆች እና በጤናማ አስተዳደግ መካከል፣ በልጆች እና በማህበራዊ ህይወት መካከል ጣልቃ የገባው ጠላት ስልክ ነው። አካላዊ ቅጣት የሚታይ እና የሚዳሰስ ቢሆንም በሞባይል ስልክ እና በመሰሎቹ የሚደርሰው ጉዳት በወቅቱ የማይታይ እና የማይዳሰስ የአአምሮ እና የአካላዊ ጤና ጉዳት ነው። ስልክ ልጆችን ያለምንም ገመድ አስሮ የሚያቀምጥ ነገር ነው። ብዙ ወላጆችም ልጆቻቸው ሲሯሯጡ እና ሲረብሹ ስልክ በመስጠት ያስቀምጧቸዋል።ማወቅ ያለብን፦ስልክም ሆነ ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ቴሌቪዝንን ጨምሮ ለልጆች አካላዊ እና ማህበራዊ ጤና ጠንቅ መሆናቸውን ነው። ማውቅን ያለብን፦ በተለይ ከሶስት አመት በታች ላሉ ሕጻናት ስልክ በመስጠት ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ይበልጣል።ማወቅ ያለብን፦ መቼ እና እንዴት መስጠት እንደሚገባ ነው። ማወቅ ያለብን፦ ስልክም ሆነ ቴሌቪዝን ልጆችን ከወላጆች፣ ክማህበረሰቡ ይልቁንም ከራስቸው እንድሚያራርቃቸው ነው።ማውቅ ያለብን፦ ስልክም ሆነ ቴሌቪዝን በአግባቡ ከተጠቀመንበት ጠቃሚ መሆኑን ነው። ስልክ ለልጆች መቼ መሰጠት አለበት? ሆስፒታል- ለክትባትም ሆነ ለህክምና ልጆች ሲሄዱ በስልክ እንዲጫወቱ ማድረግ ለወላጅም ለልጅም እረፍት የሚስጥ ነገር ነው። ሆስፒታል ውስጥ ሲሯሯጡ ከሚመጣው ጭንቀት እና ረብሻ ይታደጋቸዋል። ለጉብኝት ወይም ዘመድ ጥየቃ ፦ በዚህ ጊዜ በተለይ ልጆች የሌሉበት እና ለእነሱ የሚሆን ነገር በሌለበት ቦታ ስልክ መስጠት ለወላጆችሁም ለልጆችም ጥቅም አለው። ወላጆች ጉዳያቸውን በእርጋታ ይጨርሳሉ። ልጆችም ሳይሰላቹ እና ሳይበሳጩ ይቆያሉ። ረዥም ጉዞ ሲያደርጉ፣ እናት ወይም አባት የቤት ስራ በሚሰሩበት ጊዜ በተለይ ደግሞ ምግብ በሚያበስሉበት እና በሚያፀዱበት ጊዜ። በሰንበት ቀናት፣ በበአኣላት ወይም ልጆች ጥሩ ነገር ሲሰሩ እንድ ሽልማት። ማውቅ ያለብን፦ ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ በተለይ ስልክ በቀን ከሁለት ሰአት በላይ እንዲጠቀሙ ማድረግ አደጋ አለው። አአምሯዊ ቅጣት ይሆናል